ለ2017 STEM ክረምት ተማሪዎች በሙሉ፣
የSTEM ክረምት ስልጠና ነሐሴ 26, 2017 እንደሚጠናቀቅ እና የማጠቃለያ ፈተና ነሐሴ
27 እና 28,2017 እንደሚሰጥ እያሳወቅንን፥ የማጠቃለያ የሽኝት ፕሮግራማችን ደግሞ ጳጉሜ 01, 2017 የሚካሄድ
መሆኑን እየገለፅን፣ ለፈተናው አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ አጥብቀን እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ፥
ያለ በቂ ምክንያት ፈተና የማይወስድ ወይም ስልጠናውን የሚያቋርጥ ማንኛውም ተማሪ፣ ወደፊት በማዕከላችን በሚዘጋጁ
ፕሮግራሞች ላይ እንደማይሳተፍ እናሳውቃለን።
የSTEM ማዕከል